የከተማዋ የህዝብ ቁጥር መጨመር ፣ የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እና የቆዳ ስፋት እያደገ በመምጣቱ እንዲሁም ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ባለጉዳዮችን በአግባቡ ለማስተናገድ በማስፈለጉ በ1909 ዓ.ም የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ተቋቋመ፡፡ በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የአዲስ አበባን ዘመናዊነት እንቅስቃሴዎች ዘላቂ ልማት ያሸጋገረበት ጊዜ ነበር፡፡ የማዘጋጃ ቤት አስተዳደር ከተቋቋመም በኋላ ሊሎ ሽፋኑ በተባለ ፈንረሳዊ እና አድለቢ በተባለ ሶሪያዊ ግፊት ማዘጋጃ ቤቱ አድዋ ሲኒማ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ እንዲመሰረት ተደረገ፡፡ ማዘጋጃ ቤቱም የከተማው “የማህበር ቤት” ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ ይህ ስያሜ የተሰጠውም ማዘጋጃ ቤቱ እንዲመሰረት ግፊት ሲያደርጉ በነበሩት በሶሪያው እድሊቢ ነው። ቀድሞ “የከተማ ማህበር ቤት”የሚለው ሰያሜ municipality የሚለው የእግንሊዘኛ ቃል አዲስ አበባን አይወክልም በሚል በህሩይ ወልደ ሥላሴ አማካኝነት በ1920 ዓ.ም ማዘጋጃ ቤት የሚል ስያሜ እንደተሰጠው በታሪክ ሰፍሯል፡፡ በወቅቱ ለአዲስ አበባ ከተማ እድገትና ለከተማዋ ህዝብ ደህንነት ሲባል በ1926 ዓ.ም የሚያከናውናቸውን ተግባራት በ16 ዋና ዋና ክፍሎች ከ250 ባልበለጡ ሰራተኞች የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ስራውን ያከናውን ነበር፡፡ የስራ ክፍሎቹም የከንቲባ ጽህፈት ቤት፣ የርስት፣ ክፍል፣ የካርታ ማንሳትና የግምት ክፍል፣ የዳኝነት ክፍል፣ የአራዳ ዘበኛ የተሽከርካሪና የመንጃ ፈቃድ /የቁማር ጨዋታ ቁጥጥር ክፍልን ጨምሮ/ የጽዳት ክፍል የገንዘብና የሥራ መቆጣጠሪያ ክፍል፣ የምስጢር ክፍል /የህክምና ክፍል /ልዩ ጓዳ/ የውል ክፍል፣ የእሳትና አደጋ መከላከል ክፍልና የጋራዥ ክፍል የተባሉት ነበር፡፡ እነዚህ የስራ ክፍሎች ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ እያንዳንዱ ክፍል ንኡስ ቅርንጫፎች ነበሩት፡፡ ማዘጋጃ ቤቱ ከላይ የተዘረዘሩት ዋና ዋና ክፍሎች ይኑሩት እንጅ ለከተማዋ እድገት የነበረው አስተዋጾኦ አመርቂ እንዳልነበር የተለያዩ ጽሁፎች ያስረዳሉ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ከከተማዋ እድገት ጋር ተያይዞ የመጣውን የነዋሪዎች ችግር ለማሻሻል እና የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አደረጃጀት እና ህንጻ በማስፈለጉ ዛሬ በማገልገል ላይ የሚገኘውን ማዘጋጃ ቤት ህንጻ እንዲገነባ ተወሰነ፡፡

ታሪክ

ያለፉት ፴ አመታት የአዲስ አበባ ከንቲቦች

ታከለ ኡማ
ታከለ ኡማ2010-2012 E.C.
ድሪባ ኩማ
ድሪባ ኩማ2005-2010 E.C.
ኩማ ደመቅሳ
ኩማ ደመቅሳ2000-2005 E.C.
ብርሃኔ ድርሳ
ብርሃኔ ድርሳ1998-2000 E.C.
አርክበ እቁባይ
አርክበ እቁባይ1995-1998 E.C.
አሊ አብዶ
አሊ አብዶ1990-1995 E.C.
ተፈራ ዋልዋ
ተፈራ ዋልዋ1985-1989 E.C.
ሙሉአለም አበበ
ሙሉአለም አበበ1985-1989 E.C.
ተጨማሪ ያንብቡ