About admin

This author has not yet filled in any details.
So far admin has created 31 blog entries.

“በአብሮነት እና በአንድነት ከተተባበርን የኢትዮጵያን ብልጽግና ከማረጋገጥ ማንም የሚያስቆመን አካል የለም “ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

2021-04-10T20:40:51+00:00

14ኛው የስልጤ የባህል ፣የቋንቋና የታሪክ እንዲሁም የራስ አስተዳደር የተመሰረተበት 20ኛ አመት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣የፌደራል እና የከተማችን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር ፣ የስልጤ ማህበረሰብ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ወዳጅነት አደባባይ ተከብሯል ።አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች አንድነት ፣ ፍቅርና ህብረብሄራዊነት ማድመቂያ ናት ያሉት ወ/ሮ አዳነች የስልጤ ብሄረሰብ ከሌሎች እህት ወንድም ህዝቦች ጋር በመሆን ከተማዋን እያለሙ ፤እያሳደጉ ይገኛሉ ብለዋል። በአብሮነት እና በአንድነት ከተሰራ በርካታ እድሎች እና ጸጋዎች አሉን ፤ ከተተባበርን እና ከተጋገዝን የኢትዮጵያን ብልጽግና ከማረጋገጥ ማንም የሚያስቆመን አካል እንደሌለ ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል ።ኢትዮጵያውንን እርስ በእርስ እንድንከፋፈል የሚያደርጉ አሉባልተኞችን ምንጫቸውን በማድረቅ [...]

“በአብሮነት እና በአንድነት ከተተባበርን የኢትዮጵያን ብልጽግና ከማረጋገጥ ማንም የሚያስቆመን አካል የለም “ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ2021-04-10T20:40:51+00:00

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለ85 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት እና ለ770 ሴቶች እና ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ 166 የመስሪያ ቦታ ሼዶችን አስረከቡ።

2021-04-10T20:37:07+00:00

በቁልፍ ርክክብ መርሐ ግብር ላይ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የከተማዋ ሀብት በእኩልነት እና በፍትሃዊነት ለህዝቡ መድረስ ይገባዋል፤ለዚህም የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።የተጀመረው የልማት እና የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን ሁሉም መተባበር እና መተጋገዝ እንደሚገባው ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቅርበዋል ። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ የመንግስት ቤቶችን በማስለቀቅ 85 ያህሉን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች እና አካል ጉዳተኞች ማስተላለፍ መቻላቸውን ገልጸዋል ። እንዲሁም ለረጅም አመታት ተደራጅተው የመስሪያ ቦታ ሼድ ለመውሰድ ሲጠባበቁ ከቆዩ የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ዜጎች በ181 ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ 770 ሴቶች እና ወጣቶች ተጠቃሚ [...]

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለ85 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት እና ለ770 ሴቶች እና ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ 166 የመስሪያ ቦታ ሼዶችን አስረከቡ።2021-04-10T20:37:07+00:00

በተለያዩ ሳይቶች በግንባታ ላይ ያሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በፍጥነት ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች እንዲተላለፉ የስራ ተቋራጮች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ ተቀመጠ ።

2021-04-10T20:27:30+00:00

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከተማዋ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመሆን በተለያዩ ሳይቶች በግንባታ ላይ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የግንባታ ሂደት በመጎብኘት ቤቶቹ በአፋጣኝ በሚያልቁባቸው ሁኔታዎች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። በጉብኝቱ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት በተለያዩ ስይቶች በግንባታ ላይ ያሉ የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን ወሳኝ የሆኑ የሳይት ስራዎች በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል ።ከሳይት ስራ በተጨማሪ የመንገድ ፣የመብራት ፣ የውሃ እና ፍሳሽ የመሳሰሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች በአብዛኛው ሳይቶች እየተሰራ ቢሆንም በአንዳንድ ሳይቶች ግን የውሃና ፍሳሽ ስራዎች ከግንባታው ጋር እኩል ባለመከናወናቸው የቤቶቹን ግንባታ እንዳዘገዩት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጠቁመዋል ።የስራ ተቋራጮቹ በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዲገቡ እና ቤቶቹን አፋጣኝ ጨርሶ [...]

በተለያዩ ሳይቶች በግንባታ ላይ ያሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በፍጥነት ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች እንዲተላለፉ የስራ ተቋራጮች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ ተቀመጠ ።2021-04-10T20:27:30+00:00

ኢትዮጵያ አሁንም ወደፊትም በአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን የሚያቅብ ማናቸውም ዓይነት ስምምነት #አትፈርምም”

2021-04-10T20:19:06+00:00

ኢትዮጵያ ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ የኮንኮ ኪንሻሳ የሶስትዮሽ ድርድር ዙሪያ መግለጫ አውጥታለች ። ከመግለጫው የተወሰደ ፦"...የታለቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዓመት ሙሌት በመርሆዎች መግለጫ መሰረት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ይከናወናል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በግድቡ የሁለተኛ ዓመት ሙሌት ዙሪያ ተገቢውን መረጃ ለመቀያየር ዝግጅቷን በተደጋጋሚ ገልፃለች። ሁለቱ ሀገሮች ስምምነት ሳይደርስ ግድቡ መሞላት የለበትም በሚል የሚቀርብ አቋም የህግ መሰረት የሌለው እንዲሁም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብቷን የመጠቀም መብት የሚጋፋ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። የግድቡ አሞላል እና ተያያዥ የውሃ አለቃቅ ስርዓት ላይ ለመስማማት ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ዝግጁ ብትሆንም ግብፅ እና ሱዳን በግድቡ ላይ የሚደረገው ድርድር እና ውጤቱ የኢትዮጵያን የውሃ ድርሻ የሚገድብ እና አለን የሚሉትን የውሃ ክፍፍል የሚያጸና አስገዳጅ ስምምነት ካልተደረሰ የሚል [...]

ኢትዮጵያ አሁንም ወደፊትም በአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን የሚያቅብ ማናቸውም ዓይነት ስምምነት #አትፈርምም”2021-04-10T20:19:06+00:00

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት አውታር ላይ ዝርፊያ ሲፈፅሙ የተገኙ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተያዙ፡፡

2021-04-10T20:11:36+00:00

ሶስቱ ግለሰቦች በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 አካባቢ መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት አውታር ላይ ዝርፊያ ሲፈፅሙ በአካባቢው ነዋሪዎች በተሠጠ ጥቆማ ተይዘዋል፡የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በላከው መረጃ በግለሰቦቹ ላይ ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል ብሏል፡፡ በዝርፊያው 2 ሺህ 250 ሜትር የመካከለኛ መስመር ማስተላለፊ መስመሮች፣ 42 የምሰሶ ስኒዎች እና አራት የእንጨት ምሶሶዎች ከጥቅም ውጭ ሆነዋል ተብሏል፡፡ በዚህ ምክንያትም በኮዬ ፈጬ ያሉ ደንበኞችና በአካባቢው የሚገኙ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ታዎሮች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ተቋርጦባቸዋል፡፡በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት አውታሩ ላይ በደረሰው የስርቆት ወንጀል ተቋሙ ከ353 ሺህ 623 ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበትም አስታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በተዘረፈው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት አውታር ምክንያት የተቋረጠውን አገልግሎት [...]

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት አውታር ላይ ዝርፊያ ሲፈፅሙ የተገኙ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተያዙ፡፡2021-04-10T20:11:36+00:00

“ሴቶች ብዙ ተግዳሮቶችን በማለፍ አቅዶ የመፈጸም አቅምን እያሳደጉ ለሀገር ልማት እና እድገት ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ” ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

2021-04-10T20:32:40+00:00

"#ትችያለሽ -በፈተና የተሞረደ ማንነት ለለውጥ የተመቸ ስብዕናን ይገነባል "በሚል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሴቶች ተሳትፎ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል ። በምክክር መድረኩ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ ፣የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ መሀመድ ፣ሴት ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ ሴት አመራሮች ተገኝተዋል ። በምክክር መድረኩ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የሴቶች የማቀድ እና የመፈጸም አቅምን እያሳደጉ ለሀገር ልማት ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ ብለዋል።በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ እየተከናወነ ባሉ ግዙፍ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በመምራትም ይሁን በመፈጸም የሴቶች ሚና ከፍተኛ ነው [...]

“ሴቶች ብዙ ተግዳሮቶችን በማለፍ አቅዶ የመፈጸም አቅምን እያሳደጉ ለሀገር ልማት እና እድገት ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ” ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ2021-04-10T20:32:40+00:00

በአዲስ አበባ ከተማ በከባድ ወንጀሎች ላይ ተሰማርተው የነበሩ 34 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

2021-04-10T20:14:36+00:00

ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ከተማዋ የደህንነት ስጋት እንዳለባት በማስመሰል የሀሰት መረጃ የሚያሰራጩ ሚዲያዎችና ማኅበራዊ አንቂዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል። ፖሊስ በቁጥጥር ስር ባዋላቸው የወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ ባደረገው ጥልቅ ምርመራ 12 ተሽከርካሪዎች ቴሌቪዥንና ኮምፒውተሮችን መያዙን ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በከባድ ወንጀሎች ላይ ተሰማርተው የነበሩ 34 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።2021-04-10T20:14:36+00:00

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው እለት ይካሂዳል፡፡

2021-04-09T12:32:02+00:00

በ8ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2013 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚያደርግ በምክር ቤቱ የፕሬስና ህዝብ ግነኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዲስ አለም እንቻለው ገልጸዋል፡፡በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ ፍርድ ቤቶች የ2013 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የሚገመግም ሲሆን ልዩ ልዩ ሹመቶችንም እንደሚያጸድቅ አቶ አዲስ አለም ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው እለት ይካሂዳል፡፡2021-04-09T12:32:02+00:00

የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮዎች በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች የጉብኝት መርሐግብር እንደቀጠለ ነው።

2021-04-09T14:45:52+00:00

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ተፎካካሪ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮዎች በከተማዋ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል ። ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ፣መኢአድ ፣የህዳሴ ፓርቲ፣የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ህብረት ፣የአዲስ ትውልድ ፓርቲ እና የሌሎች የፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የህዝብ ላይብረሪ እና የአድዋ ዐዐ ኪሎሜትር የፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮዎች በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች የጉብኝት መርሐግብር እንደቀጠለ ነው።2021-04-09T14:45:52+00:00

በቅርቡ 11ኛ ክፍለ ከተማ ሆኖ የተዋቀረው ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከነገ ጀምሮ መደበኛ አገልግሎት እንደሚሰጥ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አበሰሩ ።

2021-04-05T13:11:26+00:00

ክፍለ ከተማው በይፋ ስራ መጀመሩን አስመልክቶ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለለሚ ኩራ ነዋሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈው፣ ክፍለ ከተማው በሙሉ አቅሙ ስራ መጀመሩን በይፋ አብስረዋል::አዲሱ ክፍለ ከተማ የለውጡ ትሩፋት ነው ያሉት ወ/ሮ አዳነች የህዝብ ጥያቄ ምላሽ ያገኝ ዘንድ የሚሰራው መንግስት የብልፅግና ጎዳናን ለማስቀጠል ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል:: የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊሲዎችች በመንደፍ ተግባራዊ እንደሚደረጉ እና የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች የመመለስ ስራ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከቦሌ እና የካ ክፍለ ከተሞች 6 ነባር ወረዳዎች እና አራት አዳዲስ ወረዳዎችን በማደራጀት የአካባቢውን ነዋሪዎች እና አርሶ አደሮች የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል ።

በቅርቡ 11ኛ ክፍለ ከተማ ሆኖ የተዋቀረው ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከነገ ጀምሮ መደበኛ አገልግሎት እንደሚሰጥ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አበሰሩ ።2021-04-05T13:11:26+00:00
Go to Top